=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
- የቀደምት ሂወታቸው
- የትውልድ ቦታ
- የዘር ግንድ
- የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እናትና አባት
- የተባረከው ውልደት
- የጠቡባቸው ቀናቶች
- የአያታቸው መሞት
- ሥራ
- ከኸድጃ(ረ.ዐ) ጋር ያደረጉት ጋብቻ
- በሂራ ዋሻ ውስጥ የሚያደርጉት ልዩ የሆነ አምልኮ(ኢባዳ)
የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ውልደት በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ለነበረው አለም ብርሃን ሆኗል። የአረቢያ ምድር በሃጢያትና በጥንቆላ ፅልመት ተዘፍቆ በነበረው በዚህ በሚያስጠላ ዘመን የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በመካ ከተማ ውስጥ መወለድ ለአለም ብርሃን ሆኗል። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱት በመጀመሪያው አመል ፊል(የዝሆኖች) ጦርነት አመት በ12ኛው ረቢኡል አወል እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 570 በተወለዱ በሰባተኛው ቀን በማለዳ ፀሀይዋ ከመውጣቷ በፊት ለአሏህ ምስጋና ለማድረስ የእርድ ስነ-ስርአት ተካሄደ። ሁሉም የቁረይሽ ማህበረሰብ ወደ ድግሱ ተጠራ ፤ ሰዎቹም የልጁ ስም ማነው? ብለው በጠየቁ ጊዜ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ ሙሐመድ ሲሉ መለሱላቸው። ከተለመደው ስም አፈንግጠው ይህን ቅዱስና ልዩ የሆነ ስም ለዚህ ልጅ ለምን እንደተሰጠው ጠየቇቸው። እሳቸውም የኔ ልጅ የሙሉ አለም ምስጋና አድናቆት ይገባዋል ሲሉ መለሱላቸው። ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ማለት በጣም ምስጉን ማለት ነው። የመካ እምነተ ቢሶች ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ከአንድ ንጉስ መወለድ አለበት ሲሉ ተቃወሙ። የአሏህ ምርጫ ግን ሙሐመድ ቢን አብዱ ሏህ ነበሩ።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በጣም ደግ ለሆነችው ሐሊማ እንድታጠባቸው በአደራ መልክ ተሰጠች። ህፃኑንም ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ማጥባት በጀመረች ጊዜ የቻለችውን ያህል በሁለቱም ጡቶቿ ለማጥባት ስትሞክር እሳቸው ግን በግራ ጡቷ በፍፁም ጠብታ ታህል አይጠቡም። ይህ ነው እንግዲህ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዴት የሐሊማን ልጅ መብት ገና በህፃንነት እድሜያቸው የጠበቁት። ሁለት አመት ያህል ካጠባቻቸው ቡሃላ መልሳ ወደ እናታቸው መለሰቻቸው። ነገር ግን እናታቸው መልሰው እንደገና እስከ ስድስት አመታቸው ድረስ በዚያ ንፁህ በሆነው የአረብ ጐሳቸው ማህበራዊ አድርጋ እንድታሳድጋቸው በድጋሚ በአደራ መልክ ተሰጣት።
አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ሲሆኑ የሞቱት ነብዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የስምንት አመት እድሜ ልጅ እያሉ ነው። አያታቸው በጣም የተከበሩ የመካ መሪ እና የካዕባ ጠንካራ ጠባቂዎች ናቸው። እሳቸውም የሞቱት በ84 አመታቸው ሲሆን አያታቸው ለነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በጣም ተወዳጅና ብቸኛው የአብዱሏህና የአሚና ልጅ መልከ መልካም የሙትልጅ ስለነበሩ በጣም ጥልቅ ፍቅር ነበራቸው።
አቡጧሊብ: በጣም ተወዳጅ የሆኑት የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አጐት ናቸው። የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አያት ከመሞታቸው በፊት ለአቡጧሊብ ተንከባክቦ እንዲያሳድጋቸው በአደራ መልክ ሰጧቸው። አቡጧሊብ አሁን ሃላፊነቱ ተቀብለው ተንከባክበውና ማህበራዊ አድርገው በጥልቅ ፍቅርና ውዴታ አሳደጓቸው። በዚህ ጊዜ ነበር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የንግድን ጥበብ የተማሩት።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ወጣት ሲሆኑ በቤተሰብ ስራ ላይ አዘነበሉ። ነገር ግን ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም። ታላቇ ሴት ኸድጃ በጣም ሃብታም ነጋዴ ስትሆን ለተወሰነ ጊዜ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የንግድ ሸቀጦችን በአደራ መልክና በተቆጣጣሪነት በአጐታቸው በኩል የተሰጡ ሲሆን ኸድጃም በታማኝነታቸው ፣ ባማረ ስብዕናቸው ፣ በኑሮ ዘዴያቸው ፣ በግብይት ስርአታቸውና ከሰው ጋር ባለቸው ቅርርብ ትደመም ነበር። እናም እሷ እራሷ ለንግድ ሸቀጦቿን ይዘውላት እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው። አብዛኛውን ስራዎቿን ለሳቸው ሰጠች። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከዚህ ብኋላ ታማኝና ታላቅ የንግድ ሰው ሆኑ። በንግዳቸውም ብዙ ማትረፍ ጀመሩ። ኸድጃም በታላቅነታቸው ፣ በታማኝነታቸው ፣ በግብይት ስርአታቸው መደመሟን ቀጥላለች።
የኸድጃ(ረ.ዐ) አገልጋይ የነበረው መይስራህ በግብይት ወቅት ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጋር ይሆን ነበርና ሁልጊዜም ለኸድጃ የረሱልን ታላቅ ባህሪ ፣ ለጋስነትና ጨዋነት ይተርክላት ነበር። ይህን ድንቅ ያማረና ታላቅ ስብዕናና ቅድስና በመስማት ኸድጃ(ረ.ዐ) ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ለጋብቻ ጠየቀች። በጋብቻው ወቅት ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የ25 አመት መልከመልካም ወጣት የነበሩ ሲሆን ኸድጃ(ረ.ዐ) ደግሞ 40 አመቷ ነበር። ከነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር ከተጋባች ለ25 አመት ያህል ኑራለች። ይህን ተከትሎም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የጠቅላላ ስራዎቿ ተቆጣጣሪ ሆኑ። ሁሉንም ጊዜያቸውን ኃያሉ አሏህን በመገዛትም ያሳልፉ ነበር።
የመካ ሙሽሪኮች እምነተ ቢሶች ነብዩ ሙሐመድን(ሰ.ዐ.ወ) ተስፋ ለማስቆረጥ ያልጣሩትና ያላደረጉት ነገር የለም። ይሁን እንጂ በሂራ ዋሻ ጧት ማታ እዛው በመሆንና ምግብና ውሃ ይዘው በመሄድ የአምልኮት ተግባራቸውን ጀመሩ። የሂራ ዋሻ ከመካ በስተቀኝ አቅጣጫ በኩል ከሚገኘው የኑር ተራራ ላይ ያለ ሲሆን እዚህ ዋሻ ውስጥ ነበር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ያለማቇረጥ አሏህን ይገዙና ይለምኑ የነበረው። ምግብና ውሃቸው ካለላለቀ በቀር ወደ ከተማይቱ አይመለሱም።
ይቀጥላል......
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|